ጽዮንን ክበቡአት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦችዋንም ቁጠሩ፥
ለሚቀጥለው ትውልድ ትናገሩ ዘንድ፣ መከላከያ ዕርዶቿን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ መጠበቂያ ማማዎቿን እዩ።
ለሚመጣው ትውልድ ታስተላልፉ ዘንድ ጠንካራ ቅጥሮችዋን አስተውሉ፤ ምሽጎችዋንም ተመልከቱ።
በአፋቸው ሲወዱ፥ ራስዋ መንገዳቸው መሰናክላቸው ናት፥
በቅጥሮችሽ ውስጥ ሰላም፥ በግምቦችሽም ውስጥ መረጋጋት ይሁን።
እስካረጅም እስክሸመግልም ድረስ፥ ለሚመጣ ትውልድም ሁሉ ክንድህን ኃይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር ድረስ፥ አቤቱ፥ አትተወኝ።
የበዓላችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ዐይኖችህ የሰላም ማደሪያ፥ የማይወገድ ድንኳን፥ ካስማውም ለዘለዓለም የማይነቀል፥ አውታሩም ሁሉ የማይበጠስ የሆነውን ኢየሩሳሌምን ያያሉ።
ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም፦ ሰባራውን ጠጋኝ፥ የአውራ መንገድ አዳሽ ትባላለህ።
አንተም ቀንህ የደረሰብህ፥ የኃጢአትህ ቀጠሮ ጊዜ የደረሰብህ፥ ርኩስ ኃጢአተኛ የእስራኤል አለቃ ሆይ፥
ይህን ለልጆቻችሁ ንገሩ፥ ልጆቻችሁም ለልጆቻቸው፥ ልጆቻቸውም ለኋለኛው ትውልድ ይንገሩ።
“በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፥ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤
ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው፤ ቤት ስትቀመጥ፥ መንገድ ስትሄድ፥ ስትተኛና ስትነሣ ስለዚህ አጫውታቸው።