ቍጥር የሌለው ክፋት ከቦኛልና፥ ኃጢአቶቼ ያዙኝ፥ ማየትም ተስኖኛል ከራሴ ጠጉር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ አድነኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ፈጥነህ እርዳኝ።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ይሁን፥ ይሁን።
ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።
አቤቱ፥ አንተ አትጣለኝ፥ አምላኬ፥ ከኔ አትራቅ።
ዐመፃዎቼ በራሴ ላይ ከፍ ከፍ ብለዋልና፥ እንደ ከባድ ሸክምም በላዬ ከብደዋልና።
አምላክ ሆይ፥ ከእኔ አትራቅ፥ አምላኬ ሆይ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።