እጅግ ጐሰቈልሁ ተዋረድሁም፥ ሁልጊዜም በትካዜ እመላለሳለሁ።
ወገቤ እንደ እሳት ነድዷል፤ ሰውነቴም ጤና የለውም።
ትኲሳት ወገቤን እያቃጠለው ነው፤ ሁለመናዬም ጤና አጣ።
አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።
ንጉሡንም እንዲህ አልሁት፦ “ንጉሡ ለዘለዓለም ይኑር! የአባቶቼ መቃብር ያለባት ከተማ ስትፈርስ፥ በሮችዋም በእሳት ሲቃጠሉ ፊቴ ለምን አያዝን?”
ከሕመሜ ብርታት የተነሣ ልብሴ ተበላሸ፥ እንደ ቀሚስ ክሳድ ያንቀኛል።
ሥጋዬ ትልና ጓል ለብሶአል፥ ቆዳዬ ያፈከፍካል እንደገናም ይመግላል።
በመከራዬ ቀን ፊትህን ከኔ አትመልስ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ።
በላዬ በመተባበር ጠላቶቼ ሁሉ ያንሾካሽካሉ፥ በእኔ ላይም ክፋትን ያስባሉ።
ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያንጊዜ የጌታ መልአክ መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ።