መዝሙር 16:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመከረኝን አምላክ እባርካለሁ፥ ደግሞም በሌሊት ኩላሊቶቼ ይገሥጹኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚመክረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤ በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚመክረኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በሌሊት እንኳ ሕሊናዬ ያስተምረኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀኝህን ከሚቃወሟት፥ የሚያምኑብህን የሚያድናቸውን ቸርነትህን ግለጠው። |
ፍርድህን በምድር ላይ በፈረድክ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች።
የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ እንዳውቅ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም እንድትሰማ ጆሮዬን ያነቃቃል።
ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ፥ ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።