ብዙ አሕዛብን መታ፥ ብርቱዎችንም ነገሥታት ገደለ።
ብዙ ሕዝቦችን መታ፤ ኀያላን ነገሥታትንም ገደለ።
ብዙ የአሕዛብ መንግሥታትን ደመሰሰ፤ ኀያላን ነገሥታትንም ገደለ።
ከበኵራቸው ጋር ግብፅን የገደለ፥ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
እስራኤልም በሰይፍ መታው፥ ምድሩንም ከአርኖን ጀምሮ እስከ ያቦቅ እስከ አሞን ልጆች ድረስ ወረሰ፤ የአሞንም ልጆች ዳርቻ የጸና ነበረ።
ለእርሱም አንድ ሰው በሕይወት እንዳይተርፍ አድርገው እርሱንና ልጆቹን ሕዝቡንም ሁሉ ገደሉ፤ ምድሩንም ወረሱ።