ወደ ማደሪያዎቹ እንግባ፥ እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንስገድ።
“ወደ ማደሪያው እንግባ፤ እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ እንስገድ።
ከዚህ በኋላ “ኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ፤ በእግሩ ማረፊያ ሥር እንስገድ” አልን።
የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፥ ወደ እነርሱ ገብቼ ጌታን አመሰግናለሁ።
የዳዊት የዕርገት መዝሙር። ወደ ጌታ ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።
ሐሰትን የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፥ ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው ጌታ ይጸየፋል።
ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፥ በፈጠረን በእርሱ በጌታ ፊት እንበርከክ፥
ጌታ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መርገጫ ስገዱ።
ጌታ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ በቅዱስ ተራራውም ስገዱ፥ ጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።
ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ ጌታ ተራራ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
አሌፍ። ጌታ በቁጣው የጽዮንን ሴት ልጅ እንደምን አደመናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፥ በቁጣውም ቀን የእግሩን መረገጫ አላሰበም።