እነሆ፥ ጌታን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል።
እነሆ፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው፣ እንዲህ ይባረካል።
እግዚአብሔርን የሚፈራ እንደዚህ የተባረከ ይሆናል።
እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ የኃጥኣንን አንገታቸውን ቈረጠ።
ጌታን የሚፈሩትን፥ ትንንሾችንና ትልልቆችን ይባርካል።
የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ብትታዘዝ፥ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይደርሱሃል፤ አይለዩህምም።