በተጨነቅሁ ጊዜ ጌታን ጠራሁት፥ መለሰልኝ፥ አሰፋልኝም።
በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እግዚአብሔርም መለሰልኝ፤ ከመጠበብም አወጣኝ።
በተጨነቅሁ ጊዜ ጩኸቴን ወደ እግዚአብሔር አሰማሁ፤ እርሱም ሰማኝ፤ ነጻም አወጣኝ።
ሥርዐትህን እጠብቅ ዘንድ የሚቀናስ ከሆነ መንገዴ ይቅና።
ያዕቆብም እጅግ ፈራ ተጨነቀም፤ ከእርሱም ጋር ያሉትን ሰዎች፥ መንጎችን እና ከብቶችን ግመሎችንም፥ በሁለት ወገን ከፈላቸው፥
በተጨነቁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው።
በተጨነቁ ጊዜም ወደ ጌታ ጮኹ፥ ከጭንቀታቸው አዳናቸው።
የዕርገት መዝሙር። በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኽሁ፥ ሰማኝም።
በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፥ ጌታ ግን ድጋፍ ሆነኝ።
ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፥ ወድዶኛልና አዳነኝ።
የሲኦል ገመዶች ተበተቡኝ፥ የሞት ወጥመዶችም ደረሱብኝ።
መከራዬን አይተሃልና፥ ነፍሴንም ከጭንቀት አድነሃታልና በምሕረትህ ደስ ይለኛል ሐሤትም አደርጋለሁ።
በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ ቃሌም ወደ እግዚአብሔር ነው፥ እርሱም አደመጠኝ።