ዮሴፍ ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ፥ “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ይዘሃቸው ሂድ፤ ዛሬ ቀትር ላይ አብረውኝ ስለሚበሉ ፍሪዳ ተጥሎ ምሳ ይዘጋጅ” አለው።
ምሳሌ 9:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋን አዘጋጀች፥ ማዕድዋን አሰናዳች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍሪዳዋን ዐረደች፤ የወይን ጠጇን ጠመቀች፤ ማእዷንም አዘጋጀች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላዘጋጀችውም ግብዣ ፍሪዳ ዐረደች፤ የጣፈጠ የወይን ጠጅም ጠመቀች፤ ገበታም ዘርግታ ማእድ ሠራች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋንም በማድጋዋ ጨመረች። ማዕድዋን አዘጋጀች። |
ዮሴፍ ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ፥ “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ይዘሃቸው ሂድ፤ ዛሬ ቀትር ላይ አብረውኝ ስለሚበሉ ፍሪዳ ተጥሎ ምሳ ይዘጋጅ” አለው።
የሠራዊት ጌታም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ መልካምና የበሰለ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።