ምሳሌ 8:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ለሚያስተውል የቀኑ ናቸው፥ እውቀትንም ላገኟት ትክክል ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጥልቅ ለሚያስተውሉ ሁሉም ቀና ናቸው፤ ዕውቀት ላላቸውም ስሕተት የለባቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማስተዋል ላለው ሰው ሁሉም ግልጥ ነው፤ ዕውቀትም ላለው ሰው ትክክል ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሚያውቁ ፊት ሁሉ የቀና ነው፥ ዕውቀትንም ለሚያገኙ ሰዎች የቀና ነው። |
በዚያም አውራ ጎዳና ይኖራል፥ እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል፤ ንጹሐን ያልሆኑ አያልፉበትም፥ የእርሱ የሆኑ ሕዝቦች ግን ያልፉበታል፤ ተጓዦች ሆኑ፥ ሰነፎች እንኳ አይስቱበትም።
የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ይህ መባል አለበትን? በውኑ የጌታ መንፈስ ይቆጣልን? ሥራዎቹስ እነዚህ ናቸውን? ቃሎቼስ በቅን ለሚሄድ መልካም ነገር አያደርጉምን?