ምሳሌ 5:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጉድጓድህ ውኃ፥ ከምንጭህም የሚፈልቀውን ውኃ ጠጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከገዛ ማጠራቀሚያህ ውሃ፣ ከገዛ ጕድጓድህም የሚፈልቀውን ውሃ ጠጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከራስህ ጒድጓድና ምንጭ ውሃ ጠጥተህ እንደምትረካ፥ ለሚስትህ ታማኝ በመሆንና እርስዋን ብቻ በመውደድ እርካ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከማድጋህ ውኃ፥ ከምንጭህም የሚፈልቀውን ውኃ ጠጣ። |
ሕዝቅያስን አትስሙ፤’ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ‘ከእኔ ጋር ታረቁ ወደ እኔም ኑ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፥ ከጉድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ፤