ምሳሌ 4:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፍ ከፍ አድርጋት፥ እርሷም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፥ ብታቅፋትም ታከብርሃለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክብርን ስጣት፤ ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ ዕቀፋት፤ ታከብርሃለች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብን አክብራት፤ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ አጥብቀህም ብትይዛት፥ ክብርን ትሰጥሃለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠብቃት፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ አክብራት፥ እርስዋም ታቅፍሃለች። |
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤’ አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ ከእኔ ይራቅ።