ምሳሌ 26:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዲያና ወዲህ እንደሚበርር ድንቢጥ ወይም ጨረባ፥ እንዲሁም ከንቱ እርግማን በማንም ላይ አይደርስም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክንፎቿን እንደምታርገበግብ ድንቢጥ ወይም ቱር እንደምትል ጨረባ፣ ከንቱ ርግማንም በማንም ላይ አይደርስም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወፎች ወዲያና ወዲህ ሲበርሩ ምንም ጒዳት ሊያደርሱብህ እንደማይችሉ ሁሉ ከንቱ ርግማንም ምንም ጒዳት አያመጣብህም። |
መንግሥቱን የወሰድክበትን የሳኦልን ቤተሰቡ ደም ሁሉ ጌታ ወደ አንተው እየመለሰው ነው። ጌታ መንግሥትህን ለልጅህ ለአቤሴሎም አሳልፎ ሰጥቶታል፤ አንተ የደም ሰው ስለሆንህ እነሆ፥ መጥፊያህ ደርሶአል።”
ይህም ደግሞ የእስራኤልን ልጆች በምግብና በውኃ ስላልተቀበሉአቸውና እንዲረግማቸውም በለዓምን ስለ ገዙት ነው፤ ነገር ግን አምላካችን እርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው።