ቅን ነገርን ያደርጉ ዘንድ አይወድዱምና የኀጥኣን ንጥቂያ ራሳቸውን ያጠፋቸዋል።
ክፉዎችን ዐመፃቸው ይጠራርጋቸዋል፤ ቅን ነገር ማድረግ አይወድዱምና።
ዐመፀኞች መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ ስለማይወዱ በግፍ ሥራቸው ይጠፋሉ።
ጽድቅን ያደርጉ ዘንድ አይወድዱምና የኃጥኣን ጥፋት ከሩቅ ይመጣል።
ጉድጓድን ማሰ ቈፈረም። በሠራውም ጉድጓድ ይወድቃል።
አሕዛብ በሠሩት ጉድጓድ ወደቁ፥ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች።
በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው፥ የክፉዎች አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል።
ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ጽድቅን ክብርንም ያገኛል።
የኤፍሬምንም ዘር ሁሉ፥ ወንድሞቻችሁን ሁሉ እንደ ጣልሁ፥ እንዲሁ ከፊቴ እጥላችኋለሁ።
አባቱ ግን ፈጽሞ በድሎአልና፥ ወንድሙንም ቀምቶአልና፥ በሕዝቡም መካከል ክፉን ነገር አድርጎአልና እነሆ፥ እርሱ በበደሉ ይሞታል።
ፍርድን ወደ እሬት የምትለውጡ፥ ጽድቅንም በምድር ላይ የምትጥሉ እናንተ ሆይ!
ከዚህ የተነሣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣልና ማንም በከንቱ ንግግር አያታላችሁ።