ምሳሌ 17:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሽማግሌዎች አክሊል የልጅ ልጆች ናቸው፥ የልጆችም ክብር አባቶቻቸው ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልጅ ልጆች ለአረጋውያን ዘውድ ናቸው፤ ወላጆችም ለልጆቻቸው አለኝታ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሸመገሉ ሰዎች በልጅ ልጆቻቸው እንደሚመኩ ልጆችም በአባቶቻቸው ይመካሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሽማግሌዎች አክሊል የልጅ ልጆች ናቸው፤ የልጆችም ክብር አባቶቻቸው ናቸው። |
ይሁን እንጂ ከእርሱ በኋላ በኢየሩሳሌም እንዲነግሥና ኢየሩሳሌምንም በሰላም እንዲጠብቅ ጌታ አምላኩ ስለ ዳዊት ሲል ለአቢያ አንድ ወንድ ልጅ ሰጠው።
“ስሜን የምትንቁ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባርያም ጌታውን ያከብራል፥ እኔ አባት ከሆንሁ መከበሬ የት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ?” ይላችኋል የሠራዊት ጌታ። እናንተም፦ “ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?” ብላችኋል።