ክፉ ሰው የበደለኛን ከንፈር ይሰማል፥ ሐሰተኛም ወደ ተንኰለኛ ምላስ ያደምጣል።
እኩይ ሰው ክፉ ንግግር ያዳምጣል፤ ሐሰተኛም የተንኰለኛን አንደበት በጥንቃቄ ይሰማል።
ክፉ ሰዎች ክፉ ነገርን ይሰማሉ፤ ሐሰተኞችም ሐሰትን ያዳምጣሉ።
ክፉ ሰው ከሕግ ውጭ የሆኑትን ሰዎች አንደበት ይሰማል፤ ጻድቅ ግን የሐሰት ከንፈሮችን አይመለከትም። ለሚያምን በዓለም ያለው ገንዘቡ ነው፥ ለማያምን ግን መሐለቅ የለውም፥
እግዚአብሔር ለጠማማ ሰው አሳልፎ ሰጠኝ፥ በክፋዎችም እጅ ጣለኝ።
የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፥ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል።
ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያመሰግናሉ፥ ሕግ ጠባቂዎች ግን ይቃወሟቸዋል።
ባለ ራእዮችን፦ “አትመልከቱ” ይላሉ፥ ነቢያትንም፦ “ጣፋጩንና አታላዩን ነገር እንጂ ቅኑን ነገር አትንገሩን፤
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ወድደዋል፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ ዓለምም ይሰማቸዋል።