ምሳሌ 10:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታን መፍራት ዘመንን ታረዝማለች፥ የከፉዎች ዕድሜ ግን ታጥራለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፤ የክፉዎች ዕድሜ ግን በዐጭር ይቀጫል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፤ ክፉዎች ግን ያለ ዕድሜያቸው በሞት ይቀጫሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን መፍራት ዘመንን ያረዝማል፤ የኃጥኣን ዕድሜ ግን ያጥራል። |
ያልወለደችውን እንደምታቅፍ ቆቅ፥ ባለጠግነትንም በቅን ባልሆነ መንገድ የሚሰበስብ ሰው እንዲሁ ነውና፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፥ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።