ዘኍል 7:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በካህኑም በአሮን ልጅ በኢታምር ቁጥጥ ሥር ሆነው ለሜራሪ ልጆች እንደ አገልግሎታቸው አራት ሰረገሎችንና ስምንት በሬዎችን ሰጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሜራሪያውያንም ለአገልግሎታቸው በሚያስፈልጋቸው መጠን አራት ሠረገሎችና ስምንት በሬዎች ሰጠ። እንግዲህ እነዚህ ሁሉ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር ኀላፊነት የሚመሩ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሜራሪያውያን አራት ሠረገሎችንና ስምንት በሬዎችን ሰጠ። የእነርሱም አገልግሎት የሚከናወነው የአሮን ልጅ በሆነው በኢታማር ኀላፊነት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከካህኑም ከአሮን ልጅ ከኢታምር እጅ በታች ላሉት ለሜራሪ ልጆች እንደ አገልግሎታቸው መጠን አራት ሰረገሎችንና ስምንት በሬዎችን ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከካህኑም ከአሮን ልጅ ከኢታምር እጅ በታች ላሉት ለሜራሪ ልጆች እንደ አገልግሎታቸው አራት ሰረገሎችንና ስምንት በሬዎችን ሰጣቸው። |