ዘኍል 6:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ያምጣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በስምንተኛው ቀን ሁለት ዋኖስ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ይዞ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ዘንድ ያምጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስምንተኛው ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት ርግቦች በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደሚገኘው ካህን ያምጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ያምጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ያምጣ፤ |
“የመንጻትዋ ወራትም በተፈጸመ ጊዜ፥ ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአንድ ዓመት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ የርግብም ግልገል ወይም ዋኖስ ለኃጢአት መሥዋዕት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታምጣ።