ሌዋውያንም ዕድሜአቸው ሠላሳ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ተቈጠሩ፤ በእያንዳንዳንዱ ነፍስ ወከፍ ተቈጠሩ፤ ድምራቸውም ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበር።
ዘኍል 4:48 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱ የተቈጠሩት ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቍጥራቸው ስምንት ሺሕ ዐምስት መቶ ሰማንያ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠቅላላ ቊጥራቸው ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሰማኒያ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱ የተቈጠሩት ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱ የተቈጠሩት ስምንት ሺህ ኣምስት መቶ ሰማንያ ነበሩ። |
ሌዋውያንም ዕድሜአቸው ሠላሳ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ተቈጠሩ፤ በእያንዳንዳንዱ ነፍስ ወከፍ ተቈጠሩ፤ ድምራቸውም ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበር።
በጌታ ትእዛዝ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ ከሌዋውያን ወንዶች ሁሉ ዕድሜው አንድ ወር የሞላውና ከዚያም በላይ ያለው በየወገናቸው የተቈጠሩት ሁሉ ሀያ ሁለት ሺህ ነበሩ።
በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራውን ለመሥራትና ዕቃውን ለመሸከም የገቡት ሁሉ፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉት፥