ዘኍል 4:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንዲሁም የጌድሶንን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች በየወገኖቻቸውም የሕዝብ ቈጠራ አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጌርሶናውያንንም በየቤተ ሰባቸውና በየጐሣቸው ቍጠራቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የጌርሾን ጐሣዎች የሆኑትን ሌዋውያን በየትውልዳቸውና በየቤተሰባቸው ቊጠራቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የጌድሶንን ልጆች ከመጀመሪያው ጀምረህ በየአባቶቻቸው ቤቶች በየወገኖቻቸውም ቍጠራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጌድሶንን ልጆች ድምር ደግሞ በየአባቶቻቸው ቤቶች በየወገኖቻቸውም ውሰድ። |
በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቁጠራቸው።