ዘኍል 35:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውንም ለሞት በሚያበቃው በእጁ ባለው በእንጨት መሣርያ ቢመታው የተመታውም ቢሞት፥ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳዩም ፈጽሞ ይገደል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይም አንድ ሰው መግደል የሚችል ዕንጨት በእጁ ቢይዝና ሌላውን ሰው እንዲሞት ቢመታው ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በሞትም ይቀጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው ሌላውን ሰው ሊገድል በሚችል የእንጨት መሣሪያ መትቶ ቢገድለው ያ ሰው ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳዩም ይገደል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም በሚሞትበት በእጁ ባለው በእንጨት መሣሪያ ቢመታው፥ የተመታውም ቢሞት፥ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳዩም ፈጽሞ ይገደል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም በሚሞትበት በእጁ ባለው በእንጨት መሣርያ ቢመታው የተመታውም ቢሞት፥ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳዩም ፈጽሞ ይገደል። |