ዘኍል 31:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከየነገዱ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦርነት ላኩ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ አንዳንድ ሺሕ ሰው ለጦርነቱ ላኩ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንዳንድ ሺህ ወንዶችን መርጣችሁ ወደ ጦርነቱ ላኩ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦርነት ስደዱ፤” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከየነገዱ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦርነት ስደዱ ብሎ ተናገራቸው። |
ሙሴም ሕዝቡን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ “ከእናንተ መካከል ሰዎች ለጦርነት የተዘጋጁ ይሁኑ፤ ስለ ጌታ በቀል ምድያምን እንዲበቀሉ በምድያም ላይ ይዝመቱ፤
ጌታም ጌዴዎንን፦ ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፥ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።
ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፤ ወደነዚያ ያልተገረዙ ሰዎች ጦር ሰፈር እንሻገር፤ ምናልባትም ጌታ ይዋጋልን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት ለማዳን ጌታን የሚያግደው የለምና” አለው።