ለጌታም ቤት አገልግሎት የመገናኛውን ድንኳን ሥርዓት የመቅደሱንም ሥርዓት የወንድሞቻቸውንም የአሮንን ልጆች ሥርዓት በመጠበቅ ያገለግሉ ነበረ።”
ዘኍል 31:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ ከሰዎች ከበሬዎችም ከአህዮችም ከበጎችም ከከብቶችም ሁሉ ከኀምሳ አንድ ትወስዳለህ፥ የጌታንም ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ደግሞ ከሰውም ይሁን ከቀንድ ከብት፣ ከአህያ፣ ከበግ፣ ከፍየል ወይም ከሌሎች እንስሳት ከየዐምሳው አንዳንድ መርጠህ፣ የእግዚአብሔርን ማደሪያ ድንኳን በኀላፊነት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ስጣቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለቀሩት የማኅበሩ አባላት ከተሰጠውም ክፍል ከኀምሳ እስረኞች አንዱን፥ በዚሁ መጠን ከከብቱ፥ ከአህዮቹ፥ ከበጎቹና ከፍየሎቹ ለይታችሁ ለተቀደሰው ድንኳን ኀላፊዎች ለሆኑት ሌዋውያን ስጡ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ እኩሌታ፥ ከሰዎችም፥ ከበሬዎችም፥ ከበጎችም፥ ከአህዮችም፥ ከእንስሶችም ሁሉ ከአምሳ አንድ ትወስዳለህ፤ የእግዚአብሔርንም ድንኳን ሥርዐት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ ከሰዎች ከበሬዎችም ከአህዮችም ከመንጎችም ከከብቶችም ሁሉ ከአምሳ አንድ ትወስዳለህ፥ የእግዚአብሔርንም ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ። |
ለጌታም ቤት አገልግሎት የመገናኛውን ድንኳን ሥርዓት የመቅደሱንም ሥርዓት የወንድሞቻቸውንም የአሮንን ልጆች ሥርዓት በመጠበቅ ያገለግሉ ነበረ።”
ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ጉባኤ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ ሌዋውያን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይስፈሩ፤ ሌዋውያንም የምስክሩን ማደሪያ ይጠብቁ።”
ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ ካህናቱም የሚገለገሉባቸውን የመቅደሱን ዕቃዎች፥ መጋረጃውንም፥ መገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ።
ከእነዚያም ወደ ጦርነት ወጥተው ከተዋጉት ወታደሮች ድርሻ፥ ከሰዎችም ከበሬዎችም ከአህዮችም ከበጎችም ከአምስት መቶ አንድ ለጌታ ግብር አውጣ።
ወንድሞቻቸው የተሰጣቸውን ግዴታ እንዲወጡ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይርዱአቸው እንጂ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩ። በየአገልግሎታቸው በመደልደል በሌዋውያን ላይ እንዲሁ ታደርጋለህ።”
በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም። እነርሱ እንደሚጠየቁበት አድርገው ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ፤ ይህንንም በደስታ እንጂ በኀዘን እንዳያደርጉት፥ አለበለዚያ አይጠቅማችሁም።