ዘኍል 30:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ባልዋ የሞተባት ወይም ከባልዋ የተፋታች ሴት ግን ስእለትዋ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸኑባታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ባሏ የሞተባት ወይም ከባሏ የተፋታች ሴት የትኛውም ስእለቷ ወይም የገባችበት ግዴታ ሁሉ የጸና ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባልዋ የሞተባት ሴት ወይም ከባልዋ የተፋታች ሴት ማንኛቸውንም ስእለት ሆነ ወይም ከአንድ ነገር ለመከልከል የገባችውን ቃል መፈጸም አለባት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ባልዋ የሞተባት ወይም የተፋታች ግን ስእለቷና ራስዋን ያሰረችበት መሐላ ይጸኑባታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባልዋ የሞተባት ወይም የተፋታች ግን ስእለትዋ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ይጸኑባታል። |
ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ በእርሷ ላይ ያለውን ስእለትዋን ከአንደበትዋም በችኮላ ተናግራ ራስዋን በመሐላ ያሰረችበትን ነገር ከንቱ ያደርገዋል፤ ጌታም ይቅር ይላታል።