ዘኍል 26:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየወገናቸው የዛብሎን ወገኖች እነዚህ ናቸው፤ ከሴሬድ የሴሬዳውያን ወገን፥ ከኤሎን የኤሎናውያን ወገን፥ ከያሕልኤል የያሕልኤላውያን ወገን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዛብሎን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሴሬድ በኩል፣ የሴሬዳውያን ጐሣ፤ በኤሎን በኩል፣ የኤሎናውያን ጐሣ፣ በያሕልኤል በኩል፣ የያሕልኤላውያን ጐሣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዛብሎን ነገድ ተወላጆች ሴሬድ፥ ኤሎን ያሕይኤልና ተወላጆቻቸው ናቸው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአሮሐድ የአሮሐዳውያን ወገን፥ ከአሩሔል የአሩሔላውያን ወገን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዛብሎን ወገኖች በየወገናቸው፤ ከሴሬድ የሴሬዳውያን ወገን፥ ከኤሎን የኤሎናውያን ወገን፥ ከያሕልኤል የያሕልኤላውያን ወገን። |
“የዛብሎን ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥