ዘኍል 26:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየወገናቸው የስምዖን ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከነሙኤል የነሙኤላውያን ወገን፥ ከያሚን የያሚናውያን ወገን፥ ከያኪን የያኪናውያን ወገን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የስምዖን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በነሙኤል በኩል፣ የነሙኤላውያን ጐሣ፤ በያሚን በኩል፣ የያሚናውያን ጐሣ፤ በያኪን በኩል፣ የያኪናውያን ጐሣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የስምዖን ነገድ ተወላጆች፦ ነሙኤል፥ ያሚንና፥ ያኪን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የስምዖንም ልጆች በየወገናቸው፤ ከናሙሄል የናሙሄላውያን ወገን፥ ከኢያሚን የኢያሚናውያን ልጆች ወገን፥ ከያክን የያክናውያን ልጆች ወገን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የስምዖን ልጆች በየወገናቸው ከነሙኤል የነሙኤላውያን ወገን፥ ከያሚን የያሚናውያን ወገን፥ ከያኪን የያኪናውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን፥ |
ሑራም ከነሐስ የተሠሩትን ሁለት ምሰሶዎች በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ፊት ለፊት አቆማቸው፤ ከቤተ መቅደሱ መግቢያ በር በስተ ደቡብ በኩል የቆመው ምሰሶ “ያኪን” ተብሎ ተጠራ፤ በስተ ሰሜን በኩል የቆመው ምሰሶ ደግሞ ቦዔዝ ተባለ።
የአባቶቻቸው ቤት አለቆች እነዚህ ናቸው። የእስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል ልጆች ሐኖክ፥ ፋሉ፥ ሔፅሮንና ካርሚ፤ እነዚህ የሮቤል ወገኖች ናቸው።
“የስምዖን ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደየስማቸው ቍጥር፥ አንድ በአንድ የተቈጠሩት፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን ወንድ ሁሉ፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥