ዘኍል 22:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “በውኑ አንተን ለመጥራት አላክሁብህምን? ለምንስ ወደ እኔ አልመጣህም? በውኑ አንተን ለማክበር እኔ አልችልምን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባላቅ በለዓምን፣ “በቶሎ እንድትመጣ ልኬብህ አልነበረምን? ለምን አልመጣህም? በርግጥ ወሮታህን ልከፍል የማልችል ሆኜ ነውን?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባላቅ በለዓምን “በመጀመሪያ ሰዎች በላክሁብህ ጊዜ ስለምን አልመጣህም? አንተን ለማክበር የማልችል መስሎህ ነውን?” ሲል ጠየቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባላቅም በለዓምን፥ “አንተን ለመጥራት የላክሁብህ አይደለምን? ለምንስ ወደ እኔ አልመጣህም? አንተን ለማክበር እኔ አልችልምን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላቅም በለዓምን፦ በውኑ አንተን ለመጥራት አልላክሁብህምን? ለምንስ ወደ እኔ አልመጣህም? በውኑ አንተን ለማክበር እኔ አልችልምን? አለው። |
በለዓምም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፤ በውኑ እኔ አሁን አንዳችን ነገር ለመናገር እችላለሁን? እግዚአብሔር በአፌ የሚያድርገውን ቃል እርሱን እናገራለሁ።”
እንግዲህ አሁን ወደ ስፍራህ ሽሽ፤ እኔም እንዲህ አልሁ፦ ‘በእውነት አከብርህ ዘንድ ወድጄ ነበር፤’ ጌታ ግን፥ እነሆ፥ ክብርህን ከለከለህ።”