ዘኍል 22:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በለዓምም አህያይቱን፦ “ስላላገጥሽብኝ ነው፤ በእጄስ ሰይፍ ቢኖር አሁን በገደልሁሽ ነበር” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በለዓምም መልሶ አህያዪቱን፣ “ስላላገጥሽብኝ ነዋ! በእጄ ሰይፍ ይዤ ቢሆን ኖሮ አሁኑኑ በገደልሁሽ ነበር” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በለዓምም “እጅግ ስለ ተጫወትሽብኝ ነዋ! ሰይፍ ቢኖረኝማ አሁን በገደልኩሽ ነበር!” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በለዓምም አህያዪቱን፥ “ስለዘበትሽብኝ ነው፤ በእጄስ ሰይፍ ቢኖር አሁን በገደልሁሽ ነበር” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በለዓምም አህያይቱን፦ ስላላገጥሽብኝ ነው፤ በእጄስ ሰይፍ ቢኖር አሁን በገደልሁሽ ነበር አላት። |
ለሁሉም አንድ ዓይነት ዕጣ ክፍል መኖሩ ከፀሐይ በታች በሚደረገው ነገር በሙሉ ይህ ክፉ ነው፥ ደግሞም የሰው ልጆች ልብ በክፋት ተሞልታለች፥ በሕይወታቸውም ሳሉ እብደት በልባቸው ውስጥ ይኖራል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።
አህያይቱም በለዓምን እንዲህ አለችው፦ “ከብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ ማድረግ ልማዴ ነበረን?” እርሱም፦ “እንዲህ አላደረግሽብኝም” አላት።