ዘኍል 22:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም መልአክ ወደ ፊት ሄደ፥ በቀኝና በግራ መተላለፊያ በሌለበት በጠባብ ስፍራ ቆመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ ፊት ሄድ ብሎ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ መተላለፊያ በሌለበት ጠባብ ቦታ ላይ ቆመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም መልአኩ ወደ ፊት ቀድሞ ሄደና በግራም ሆነ በቀኝ መተላለፊያ በሌለበት ጠባብ ቦታ ላይ ቆመ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ ፊት ሄደ፤ በቀኝና በግራ መተላለፊያ በሌለበት በጠባብ ስፍራ ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ ፊት ሄደ፥ በቀኝና በግራ መተላለፊያ በሌለበት በጠባብ ስፍራ ቆመ። |