ዘኍል 18:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእናንተ ከሆነው ስጦታ ሁሉ፥ ከተመረጠው ከእርሱም ከተቀደሰው ድርሻ ሁሉ፥ የጌታን የስጦታ ቁርባን ሁሉ ታቀርባላችሁ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምትቀበሉት ሁሉ ምርጥና እጅግ የተቀደሰውን ክፍል የእግዚአብሔር ድርሻ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት ከምትቀበሉት በረከት ሁሉ በተለይ ምርጥ የሆነ ነገር መሆን አለበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከምትቀበሉት ስጦታ ሁሉ፥ ከተመረጠው ከተቀደሰውም ድርሻ ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን የመጀመሪያ መባ ሁሉ ታቀርባላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምትቀበሉት ስጦታ ሁሉ፥ ከተመረጠው ከተቀደሰውም ድርሻ ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን የማንሣት ቍርባን ሁሉ ታቀርባላችሁ። |
የማንሣት ቁርባን ነውና ከእስራኤል ልጆች ዘንድ የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይሁን፤ የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት የሰላም መሥዋዕታቸው የማንሣት ቁርባን ይሆናል፤ ለጌታ የማንሣት ቁርባን ይሆናል።
እንዲሁ እናንተ ደግሞ ከእስራኤል ልጆች ከምትቀበሉት አሥራት ሁሉ ለጌታ እንደ ስጦታ የሚቀርበውን ቁርባን ታቀርባላችሁ፤ ከእርሱም የጌታን የስጦታ ቁርባን ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ።
ስለዚህ እነርሱን እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘ከእርሱ የተመረጠውን ባቀረባችሁ ጊዜ ከአውድማው እህልና ከወይን መጭመቂያው እንደ ተገኘ ምርት ለሌዋውያን ይቈጠራል።