Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 45:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አባታችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ይዛችሁም ወደ እኔ ኑ፥ እኔም የግብጽን ምድር በረከት ሁሉ እሰጣችኋለሁ፥ የምድሪቱንም ስብ ትበላላችሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚያም አባታችሁንና ቤተ ሰባችሁን ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም እጅግ ለም ከሆነው የግብጽ ምድር እሰጣችኋለሁ፤ በምድሪቱ በረከት ደስ ብሏችሁ ትኖራላችሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 አባታቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ይምጡ፤ እኔም በግብጽ አገር ለም የሆነውን ቦታ መርጬ እሰጣቸዋለሁ፤ በቂ ምግብ አግኝተው በደስታ መኖር ይችላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አባ​ታ​ች​ሁ​ንና ንብ​ረ​ታ​ች​ሁን ሁሉ ይዛ​ችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም የግ​ብ​ፅን ምድር በረ​ከት ሁሉ እሰ​ጣ​ች​ሁ​አ​ለሁ፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ድልብ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሂዱ አባታችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ይዛችሁም ወደ እኔ ኑ እኔም የግብፅን ምድር በረከት ሁሉ እሰጣችኍለሁ፥ የምድሪቱንም ስብ ትበላላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 45:18
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔርም ከሰማይ ጠል ከምድርም ስብ የእህልንም የወይንንም ብዛት ይስጥህ፥


ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፦ “ለወንድሞችህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ይህን አድርጉ፥ ከብቶቻችሁን ጭናችሁ ወደ ከዓን ምድር ሂዱ፥


በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብጽ ሰዎች ርኩስ ነውና፥ በጌሤም እንድትቀመጡ፦ ‘እኛ አገልጋዮችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ፥ እኛም አባቶቻችንም፥ እንስሳ አርቢዎች ነን’ በሉት።”


የግብጽ ምድር በፊትህ ናት፥ በመልካሙ ምድር አባትህንና ወንድሞችህን አኑራቸው፥ በጌሤም ምድር ይኑሩ፤ ከእነርሱ መካከል ችሎታ ያላቸው ሰዎች ካሉ፥ በእኔ እንስሶች ላይ የበላይ ኀላፊዎች አድርገህ ሹማቸው።”


በወሰንሽም ሰላምን አደረገ፥ የስንዴንም ስብ አጠገበሽ።


የጌታ ጠላቶችም በተገዙለት ነበር፥ ዘመናቸውም ለዘለዓለም በሆነ ነበር፥


ለኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል ለሆነች፥ በወይን ጠጅ ለተሸነፉ፥ በለምለሙ ሸለቆአቸው ራስ ላይ ላለችም ለረገፈች ለክብሩ ጌጥ አበባ ወዮላት!


በለምለሙ ሸለቆ ራስ ላይ ያለች የረገፈች የክብሩ ጌጥ አበባ ከመከር በፊት አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች፤ያያት ሁሉ እጁን ሰዶ ይበላታል።


ለጌታ ከሚሰጡት የፍሬ መጀመሪያ ከዘይትና ከወይን ከእህልም የተመረጠውን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ።


የእናንተ ከሆነው ስጦታ ሁሉ፥ ከተመረጠው ከእርሱም ከተቀደሰው ድርሻ ሁሉ፥ የጌታን የስጦታ ቁርባን ሁሉ ታቀርባላችሁ።’


የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውንም ወተት፥ ከሰቡት በጎችና ፍየሎች ጋር፥ የባሳንንም አውራ በጎች፥ ፍየሎችም፥ ከምርጥ ስንዴ ጋር በላህ፥ ከወይኑም ዘለላ የወይን ጠጅ ጠጣህ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች