ዘኍል 12:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናቱ ሆድ በወጣ ጊዜ ግማሽ ሥጋው ተበልቶ በማኅፀን እንደ ሞተ ልጅ እርሷ እባክህ፥ አትሁን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷንም በእናቱ ማሕፀን ሳለ ሞቶ ግማሽ አካሉ ከተበላ በኋላ የተወለደ ጭንጋፍ መስላ እንድትቀር አታድርግ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋንም በእናቱ ማሕፀን ሳለ ሞቶ ግማሽ አካሉ ከተበላ በኋላ እንደ ተወለደ ጭንጋፍ እንድትመስል አታድርግ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናቱ ማኅፀን ሞቶ እንደ ተወለደ፥ ከተበላ ግማሽ ሥጋዋ ጋር ለሞት አትተዋት።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናቱ ሆድ በወጣ ጊዜ ግማሽ ሥጋው ተበልቶ እንደ ሞተ እርስዋ አትሁን። |
አሮንም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ጌታዬ ሆይ! ተሞኝተን ይህን አድርገናልና፥ ኃጢአትንም ሠርተናልና እባክህ፥ ኃጢአትን በእኛ ላይ አትቁጠርብን።
እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሞታችሁ የነበራችሁትን በደላችንን ሁሉ ይቅር ባለን ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ፤