ዘኍል 11:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ የጐመጀውን ሕዝብ በዚያ ቀብረውታልና የዚያ ስፍራ ስም ኬብሮን-ሐታማ ተብሎ ተጠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌላ ምግብ ለማግኘት የጐመጁትን ሰዎች በዚያ ስለ ቀበሯቸው የቦታው ስም “ቂብሮት ሃታአባ” ተባለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሥጋ አምሮት የሞቱትን ሕዝብ እዚያ ቀብረዋቸው ስለ ነበር የዚያ ስፍራ ስም “የምኞት መቃብር” ተባለ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጐመጁ ሕዝብ በዚያ ተቀብረዋልና የዚያ ስፍራ ስም “መቃብረ ፍትወት” ተብሎ ተጠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጐመጁ ሕዝብ በዚያ ተቀብረዋልና የዚያ ስፍራ ስም የምኞት መቃብር ተብሎ ተጠራ። |