ነህምያ 13:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ደግሞ የእስራኤልን ልጆች በምግብና በውኃ ስላልተቀበሉአቸውና እንዲረግማቸውም በለዓምን ስለ ገዙት ነው፤ ነገር ግን አምላካችን እርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ የሆነው እስራኤልን በምግብና ውሃ መስተንግዶ በመቀበል ፈንታ፣ በለዓም እንዲረግምላቸው በገንዘብ ስለ ገዙት ነበር። ይሁን እንጂ አምላካችን ርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ትእዛዝ የተሰጠበት ምክንያት እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡበት ጊዜ በጒዞ ላይ ሳሉ ሞአባውያንና ዐሞናውያን ምግብና ውሃ ስለ ከለከሉአቸው ነበር፤ ይልቁንም ይህን በማድረግ ፈንታ ለበለዓም ገንዘብ ሰጥተው የእስራኤልን ሕዝብ እንዲረግምላቸው አድርገው ነበር፤ እግዚአብሔር ግን መርገሙን ወደ በረከት ለወጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልን ልጆች በእንጀራና በውኃ አልተቀበሉአቸውምና፥ ይረግማቸውም ዘንድ በለዓምን ገዝተውባቸዋልና፤ ነገር ግን አምላካችን ርግማኑን ወደ በረከት መለሰው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልን ልጆች በእንጀራና በውኃ ስላልተቀበሉአቸውና ይረግማቸው ዘንድ በለዓምን ስለ ገዙባቸው ነው፥ ነገር ግን አምላካችን እርግማኑን ወደ በረከት መለሰው። |
ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያቀደውን፥ የቤዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትን፥ የጌታን ጽድቅ እንድታውቅ ከሺጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ የሆነውን እባክህን አስታውስ።
ንጉሡም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ለሚያንሱት ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ያደረጋችሁት ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው።’
ምክንያቱም ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በጉዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህል ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም፤ በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምም አንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዝተውት ነበር።