እንዲሁም ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማሪያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓኖቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
ነህምያ 12:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መዘምራኑም በኢየሩሳሌም ዙሪያ መንደሮች ሠርተው ነበርና ከቤትጌልገላም፥ ከጌባና ከዓዝሞት እርሻዎች ተሰበሰቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌም ዙሪያ የራሳቸውን መንደሮች ሠርተው ስለ ነበር፣ መዘምራኑን ያመጧቸው ከቤትጌልገላ፣ ከጌባዕና ከዓዝሞት አካባቢ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቤትጊልጋል፥ ከጌባዕና ከዓዝማዌት ተሰብስበው መጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቤት ጌልጋልና ከጌባ፥ ከአዝማዊትም እርሻ መዘምራኑ በኢየሩሳሌም ዙርያ ለራሳቸው መንደሮች ሠርተዋልና። |
እንዲሁም ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማሪያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓኖቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ ማዶ ፀሓይ በምትጠልቅበት አቅጣጫ ካለው መንገድ በስተ ምዕራብ በዓረባ በሚኖሩ የከነዓናውያን ምድር ውስጥ ከጌልገላ ፊትለፊት፥ በሞሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ አይደለምን?
ጌታም ኢያሱን፦ “ዛሬ የግብጽን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ” አለው፤ ስለዚህ የዚያን ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ተጠራ።