Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ዜና መዋዕል 6:60 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

60 እንዲሁም ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማሪያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓኖቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

60 ከብንያም ነገድ ድርሻ ላይ ገባዖንን፣ ጌባዕን፣ ጋሌማን፣ ዓናቶትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጡ። ለቀዓት ዘሮች የተከፋፈሉት እነዚህ ከተሞች በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

60 በብንያም ግዛትም ጌባዕ፥ ዓሌሜትና ዐናቶት ተብለው የሚጠሩት ከተሞች ከነግጦሽ ቦታዎቻቸው ለአሮን ልጆች የተሰጡ ነበሩ፤ እንግዲህ ለአሮን ዘሮች ቤተሰብ ሁሉ መኖሪያ የሚሆኑ በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

60 ከብ​ን​ያ​ምም ነገድ ጌባ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጋሌ​ማ​ት​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፥ ዓና​ቶ​ት​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን ሰጡ። ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

60 ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማርያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማርያዋን፥ ዓኖቶትንና መሰማርያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዜና መዋዕል 6:60
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉሥ ሰሎሞን ካህኑን አብያታርን፤ “ወደ ትውልድ አገርህ ወደ ዐናቶት ሂድ፤ አንተ በሞት ልትቀጣ ይገባህ ነበር፤ ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ትሸከም ስለ ነበርክ ከእርሱም ጋር የመከራው ሁሉ ተካፋይ ስለ ነበርክ እኔ አሁን አልገድልህም” አለው።


ዓሳንና መሰማሪያዋ፥ ቤት-ሳሚስና መሰማሪያዋ ናቸው፤


ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከነገዱ ወገን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተሰጡ።


እነዚህ የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤ እነርሱም ወደ መናሐትም ተማረኩ፤


መዘምራኑም በኢየሩሳሌም ዙሪያ መንደሮች ሠርተው ነበርና ከቤትጌልገላም፥ ከጌባና ከዓዝሞት እርሻዎች ተሰበሰቡ።


የጋሊም ሴት ልጅ ሆይ፤ ጩኺ! ላይሻ ሆይ፤ አድምጪ! ምስኪን ዓናቶት ሆይ፤ መልሺላት!


በብንያም አገር በዓናቶት ከነበሩ ካህናት የሆነ የኬልቅያስ ልጅ የኤርምያስ ቃላት።


በምጐበኛቸውም ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁና ማንም ከእነርሱ የሚተርፍ የለም።


ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል የርስቱን ድርሻ ከዚያ ለመቀበል ወደ ብንያም አገር ሊሄድ ከኢየሩሳሌም ወጣ።


ክፊርዓሞናይ፥ ዖፍኒ፥ ጋባ፤ ዐሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።


ዮናታን ጊብዓ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ይህን ሰሙ። ሳኦልም፥ “ዕብራውያን ይስሙት!” በማለት በሀገሩ ሁሉ መለከት አስነፋ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች