ማቴዎስ 28:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም በገዢው ዘንድ የተሰማ እንደሆነ፥ እኛ እናሳምነዋለን፤ እናንተም ከሥጋት ነጻ እንድትሆኑ እናደርጋለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ወሬ በገዥው ዘንድ ቢሰማ እንኳ፣ እኛ እናስረዳዋለን፤ ምንም ክፉ ነገር እንዳይደርስባችሁ እናደርጋለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን አገር ገዢው የሰማ እንደ ሆነ እኛ ጉዳዩን ለእርሱ አስረድተን በማሳመን በእናንተ ላይ ችግር እንዳይደርስባችሁ እናደርጋለን። ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም በገዢው ዘንድ የተሰማ እንደ ሆነ፥ እኛ እናስረዳዋለን፤ እናንተም ያለ ሥጋት እንድትሆኑ እናደርጋለን፤” አሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም በገዢው ዘንድ የተሰማ እንደ ሆነ፥ እኛ እናስረዳዋለን እናንተም ያለ ሥጋት እንድትሆኑ እናደርጋለን አሉአቸው። |