አንድ ጊዜ የአንድ ሰው ሥርዓተ ቀብር በሚፈጽምበት ሰዓት ከእነዚያ አደጋ ጣዮች መካከል አንድ ቡድን ሲመጣ ስለ ታየ፥ የሚቀበረውን ሬሳ ወደ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ በችኰላ በመወርወር ጥለውት ሸሹ፤ ያም ሬሳ ከኤልሳዕ አስከሬን ጋር በተገናኘበት ቅጽበት ወዲያውኑ ከሞት ተነሥቶ ቆመ።
ማቴዎስ 27:52 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መቃብሮችም ተከፈቱ፤ አንቀላፍተው ከነበሩት የብዙ ቅዱሳን በድን ተነሣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መቃብሮች ተከፈቱ፤ አንቀላፍተው የነበሩትም ብዙዎች ቅዱሳን ተነሡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቃብሮችም ተከፍተው ሞተው ከነበሩት ቅዱሳን ሰዎች ብዙዎች ከሞት ተነሡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መቃብሮችም ተከፈቱ፤ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤ |
አንድ ጊዜ የአንድ ሰው ሥርዓተ ቀብር በሚፈጽምበት ሰዓት ከእነዚያ አደጋ ጣዮች መካከል አንድ ቡድን ሲመጣ ስለ ታየ፥ የሚቀበረውን ሬሳ ወደ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ በችኰላ በመወርወር ጥለውት ሸሹ፤ ያም ሬሳ ከኤልሳዕ አስከሬን ጋር በተገናኘበት ቅጽበት ወዲያውኑ ከሞት ተነሥቶ ቆመ።
ሞትን ለዘለዓለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ ይህን ጌታ ተናግሮአል።
ከሲኦል እጅ እታደጋቸዋለሁ፥ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ፤ ሞት ሆይ! ቸነፈርህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ! አጥፊነትህ ወዴት አለ? ርኅራኄ ከዓይኔ ተሰወረች።
ተንበርክኮም “ጌታ ሆይ! ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር።