Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 27:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 መቃብሮችም ተከፈቱ፤ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 መቃብሮች ተከፈቱ፤ አንቀላፍተው የነበሩትም ብዙዎች ቅዱሳን ተነሡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 መቃብሮችም ተከፈቱ፤ አንቀላፍተው ከነበሩት የብዙ ቅዱሳን በድን ተነሣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 መቃብሮችም ተከፍተው ሞተው ከነበሩት ቅዱሳን ሰዎች ብዙዎች ከሞት ተነሡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 27:52
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰዎ​ችም አንድ ሰው ሲቀ​ብሩ አደጋ ጣዮ​ችን አዩ፤ ሬሳ​ው​ንም በኤ​ል​ሳዕ መቃ​ብር ላይ ጣሉት፤ የኤ​ል​ሳ​ዕ​ንም አጥ​ንት በነካ ጊዜ ሰው​ዬው ድኖ በእ​ግሩ ቆመ።


ሞት ሰዎ​ችን ዋጠ፤ በረ​ታም፤ እንደ ገናም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊት ሁሉ እን​ባን ያብ​ሳል፤ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ስድብ ከም​ድር ሁሉ ላይ ያስ​ወ​ግ​ዳል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፉ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


ሙታን ይነ​ሣሉ፤ በመ​ቃ​ብር ያሉም ይድ​ናሉ። በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ከአ​ንተ የሚ​ገኝ ጠል መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸው ነውና፤ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ምድር ታጠ​ፋ​ለህ።


ከሲ​ኦል እጅ እታ​ደ​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከሞ​ትም እቤ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሞት ሆይ! መው​ጊ​ያህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ! ድል መን​ሣ​ትህ ወዴት አለ? ደስ​ታህ ከዐ​ይ​ኖ​ችህ ተሰ​ወ​ረች።


ይህ​ንም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ነገ​ራ​ቸው፤ ከዚ​ህም በኋላ፥ “ወዳ​ጃ​ችን አል​ዓ​ዛር ተኝ​ቶ​አል፤ ነገር ግን ላነ​ቃው እሄ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው።


በጕ​ል​በ​ቱም ተን​በ​ር​ክኮ፥ “አቤቱ፥ ይህን ኀጢ​አት አት​ቍ​ጠ​ር​ባ​ቸው” ብሎ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህ​ንም ብሎ ሞተ፤ ሳው​ልም በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖስ ሞት ተባ​ባሪ ነበር።


ስለ​ዚህ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ የደ​ከ​ሙና የታ​መሙ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ብዙ​ዎ​ችም በድ​ን​ገት አን​ቀ​ላ​ፍ​ተ​ዋል።


አሁ​ንም ክር​ስ​ቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ተነ​ሥ​ቶ​አል።


እነሆ፥ አንድ ምሥ​ጢ​ርን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሁላ​ችን የም​ን​ሞት አይ​ደ​ለም።


ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና።


የምንነቃም ብንሆን፥ የምናንቀላፋም ብንሆን፥ ከእርሱ ጋር አብረን በሕይወት እንኖር ዘንድ ስለ እኛ ሞተ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች