ማቴዎስ 27:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ በርባን የሚባል በጣም የታወቀ እስረኛ ነበራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ በዐመፅ የታወቀ በርባን የሚባል እስረኛ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ “በርባን” የተባለ በዓመፀኛነቱ የታወቀ እስረኛ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜም በርባን የሚባል በጣም የታወቀ እስረኛ ነበራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም በርባን የሚባል በጣም የታወቀ እስረኛ ነበራቸው። |
ሁከት በመፍጠርና ሰውን በመግደል ምክንያት ታስሮ የነበረውን በጥያቄአቸው መሠረት አስፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን እንደ ፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው።
“እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሞት ይገባቸዋል” የሚለውን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ሕግ ቢያውቁም፥ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትንም ያበረታታሉ።
ዘመዶቼ የሆኑትና አብረውኝ ታስረው ለነበሩት ለአንድሮኒኮንና ለዩኒያን ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እነርሱ በሐዋርያት መካከል ስመጥሮችና ክርስቶስን በማመን እኔን የቀደሙ ናቸው።