ማቴዎስ 26:70 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን “የምትዪውን አላውቀውም” ብሎ በሁሉም ፊት ካደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ግን፣ “ምን እንደምትናገሪ እኔ አላውቅም” በማለት በሁላቸውም ፊት ካደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ግን “የምትዪውን አላውቅም!” ሲል በሁሉም ፊት ካደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን “የምትዪውን አላውቀውም፤” ብሎ በሁሉ ፊት ካደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን፦ የምትዪውን አላውቀውም ብሎ በሁሉ ፊት ካደ። |
ሐሰትን የተናገርሺው እኔንም ያላሰብሽው፥ በልብሽም ነገሩን ያላኖርሺው፥ ማንን ሰግተሽ ነው? ማንንስ ፈርተሽ ነው? እኔ ብዙ ጊዜ ዝም አልሁ፥ አንቺም አልፈራሽም።
ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”