ማቴዎስ 25:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አምጥቶ ‘ጌታ ሆይ! አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁ’ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐምስት ታላንት የተቀበለውም፣ ሌላ ዐምስት ተጨማሪ ታላንት ይዞ በመቅረብ፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ዐምስት ታላንት ዐደራ ሰጥተኸኝ ነበር፤ ይኸውልህ ዐምስት ተጨማሪ ታላንት አትርፌአለሁ’ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምስት መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ወደ ጌታው መጣና አምስት መክሊት አቅርቦ ‘ጌታ ሆይ! አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ! ሌላ አምስት መክሊት አትርፌአለሁ!’ አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ ‘ጌታ ሆይ! አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት፤’ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ፦ ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ። |
ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን የሆንሁትን ሆኛለሁ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋ ከንቱ አልሆነም፤ ይልቁን ከሁሉም በላይ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ሆኖም ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው።
ነገር ግን አንድ ሰው “አንተ እምነት አለህ፤ እኔ ሥራ አለኝ” ቢል፤ እምነትህን ከሥራ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ።