እውነት እላችኋለሁ፤ ባለው ነገር ሁሉ ላይ ይሾመዋል።
እውነት እላችኋለሁ፤ ባለው ንብረት ሁሉ ላይ ይሾመዋል።
በእውነት እላችኋለሁ፤ ያን አገልጋይ ጌታው በንብረቱ ሁሉ ላይ ይሾመዋል።
እውነት እላችኋለሁ፤ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል።
እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል።
አስተዋይ አገልጋይ በንጉሥ ዘንድ ይወደዳል፥ በሚያሳፍር ላይ ግን ቁጣው ይሆናል።
ጌታው ሲመጣ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባርያ የተባረከ ነው፤
ነገር ግን ያ ክፉ ባርያ ‘ጌታዬ ይዘገያል’ ብሎ በልቡ ቢያስብ፥
ጌታውም ‘መልካም፥ አንተ መልካምና ታማኝ አገልጋይ፥ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።
ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባርያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል፤ ቀርቦም ያገለግላቸዋል።
እርሱም ‘መልካም፥ አንተ በጎ አገልጋይ፥ በጥቂት ነገር የታመንህ ስለ ሆንክ በዐሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ፤’ አለው።
የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፤ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል።
ብንጸና፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤
የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማይደበዝዘውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።
ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል፤ አምላክም እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።
እኔም ድል እንደ ነሣሁ፥ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ።