Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 14:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 አስተዋይ አገልጋይ በንጉሥ ዘንድ ይወደዳል፥ በሚያሳፍር ላይ ግን ቁጣው ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ጠቢብ አገልጋይ ንጉሥን ደስ ያሰኛል፤ አሳፋሪ አገልጋይ ግን ቍጣውን በራሱ ላይ ያመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ነገሥታት ችሎታ ባላቸው አገልጋዮች ይደሰታሉ፤ አሳፋሪ አገልጋዮች ግን ንጉሡን ያስቈጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 አስተዋይ መልእክተኛ በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ነው፤ በመልካም ጠባዩም ውርደትን ከራሱ ያርቃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 14:35
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታውም ‘መልካም፥ አንተ መልካምና ታማኝ አገልጋይ፥ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።


ጌታውም ‘መልካም፥ አንተ መልካምና ታማኝ አገልጋይ፥ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።


የልብን ንጽሕናን የሚወድና ንግግሩ ለዛ ያለው ሰው፥ ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።


አስተዳዳሪ ለሐሰተኛ ነገር ትኩረት ቢሰጥ፥ ከእርሱ በታች ያሉት ሁሉ ዓመፀኞች ይሆናሉ።


ከንጉሥ ፊት ክፉ ሰዎችን አርቅ፥ ዙፋኑም በጽድቅ ትጸናለች።


ጠቢብ ንጉሥ ኀጥኣንን በመንሽ ይበትናቸዋል፥ መንኰራኵሩንም በእነርሱ ላይ ያንኰራኩርባቸዋል።


በፍርድ ወንበር የተቀመጠ ንጉሥ ክፉውን ሁሉ በዐይኖቹ ይበትናል።


አባቱን የሚያስከፋ እናቱንም የሚያሳድድ የሚያሳፍርና ጐስቋላ ልጅ ነው።


አስተዋይ ባርያ ነውረኛውን ልጅ ይገዛል፥ በወንድማማች መካከልም ርስትን ይካፈላል።


በበጋ የሚያከማች ልጅ አስተዋይ ነው፥ በመከር የሚተኛ ግን እርሱ ራሱን ያስነውራል።


ጽድቅ፥ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፥ ኃጢአት ግን ሕዝብን ታስነውራለች።


ፈርዖንም፥ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እንደዚህ ያለ ሰው ማንን ልናገኝ እንችላለን?” ብሎ ጠየቃቸው።


የጽድቅ ከንፈር የነገሥታት ደስታ ናት፥ በቅን የሚናገር እርሱንም ይወድዱታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች