ማቴዎስ 22:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አለው “‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም እንዲህ አለው፤ “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ፤’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ጌታ አምላክህን በሙሉ ልብህ፥ በሙሉ ነፍስህ፥ በሙሉ ሐሳብህ ውደድ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም እንዲህ አለው “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። |
እርሱን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም አእምሮህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ኋይልህ መውደድ፥ እንዲሁም ጐረቤትህን እንደ ራስህ መውደድ ከሚቃጠል መሥዋዕት ሁሉና ከሌሎችም መሥዋዕቶች ይበልጣል።”
እርሱም መልሶ፦ “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ፤” አለው።
“እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ ጌታ አምላክህ ከአንተ የሚፈልገው ምንድነው? ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔርን እንድትፈራው፥ በመንገዱም ሁሉ እንድትሄድ፥ ጌታ አምላክህንም እንድትወደው፥ በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ እንድታመልከው፥