ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።
ማቴዎስ 20:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አሉት ‘እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፤ የቀኑን ድካምና ሐሩር ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘እነዚህ በመጨረሻ የተቀጠሩት አንድ ሰዓት ብቻ ሲሠሩ፣ ቀኑን ሙሉ በሥራ ስንደክምና በፀሓይ ስንንቃቃ ከዋልነው ጋራ እንዴት እኩል ትከፍለናለህ?’ አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘እነዚህ በመጨረሻ መጥተው የሠሩት ለአንድ ሰዓት ብቻ ነው፤ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ በፀሐይ ሙቀት እየተቃጠልን በሥራ ስንደክም ከዋልነው ከእኛ ጋር እኩል አደረግሃቸው።’ |
ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።
“እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ “የተሰረቀውን፥ አንካሳውንና የታመመውን አምጥታችኋል፤ እንዲሁም ቁርባንን አምጥታችኋል፤ በውኑ ከእጃችሁ መቀበል ይገባኛልን?” ይላል ጌታ።
እናንተም እንዲህ ብላችኋል፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ ትእዛዙን መጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ ፊት ኀዘንተኞች ሆነን መሄድ ምን ይጠቅመናል?
ይህ የሆነው፥ አሕዛብ አብረው እንዲወርሱ፥ በአንድ አካልም አብረው እንዲሆኑ፥ በወንጌልም አማካኝነት በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነውን የተስፋ ቃል አብረው እንዲካፈሉ ነው።