ማቴዎስ 2:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ንጉሡን ከሰሙ በኋላ ሄዱ፤ እነሆ፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠቢባኑ ንጉሡ ያለውን ከሰሙ በኋላ ጕዟቸውን ቀጠሉ። ይህም በምሥራቅ ያዩት ኮከብ እየመራቸው ሕፃኑ እስካለበት ድረስ ወሰዳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም የንጉሡን ቃል ከሰሙ በኋላ፥ ወጥተው ሄዱ፤ እነሆ! በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ በነበረበት ቦታ ላይ እስኪቆም ድረስ፥ እፊት እፊታቸው እየሄደ ይመራቸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር። |
እንዲህ ብሎም ወደ ቤተልሔም ላካቸው፦ “ሂዱ፤ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ” አላቸው።
ደግሞም ይህን የበለጠ የሚያረጋግጥ የነቢያት ቃል አለ፤ ጎሕ እስኪቀድ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪገለጥ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚያስተውል ቃሉን ልብ በማለት መልካም ታደርጋላችሁ።