ማቴዎስ 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም እንዲህ አሉት፦ በይሁዳ ቤተልሔም ነው፤ በነቢዩ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “በይሁዳ ቤተ ልሔም፤ ነቢዩ እንዲህ ብሎ ጽፏልና አሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ “በነቢይ እንዲህ የሚል ትንቢት ስለ ተጻፈ፥ መሲሕ የሚወለደው በይሁዳ ምድር፥ በቤተልሔም ከተማ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም “ ‘አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና’ ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት። |
መሳፍንት ይፈርዱ በነበረበት ዘመን በአገሩ ላይ ረሀብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር በሞዓብ ምድር ለመቀመጥ ከቤተልሔም ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።
ስለዚህ ሁለቱም እስከ ቤተልሔም ድረስ ሄዱ። ወደ ቤተልሔምም በደረሱ ጊዜ፥ ያገሩ ሰዎች ሁሉ ታወኩ ስለ እነርሱ፥ ሴቶቹም፦ “ይህች ናዖሚን ናትን?” አሉ።
ከጥቂት ጊዜ በኋላም፥ ቦዔዝ ከቤተልሔም መጣ፥ አጫጆችንም፦ “ጌታ ከእናንተ ጋር ይሁን” አላቸው። እነርሱም፦ “ጌታ ይባርክህ” ብለው መለሱለት።
በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች ሁሉ፦ “እኛ ምስክሮች ነን፥ ጌታ ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ፥ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፥ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተልሔም ይጠራ።
ጌታ ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፥ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።