Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሩት 1:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 መሳፍንት ይፈርዱ በነበረበት ዘመን በአገሩ ላይ ረሀብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር በሞዓብ ምድር ለመቀመጥ ከቤተልሔም ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 መሳፍንት በሚገዙበት ዘመን፣ በምድሪቱ ላይ ራብ ሆነ፤ አንድ ሰው በይሁዳ ከምትገኘው ከቤተ ልሔም ሚስቱንና ሁለቱን ወንዶች ልጆቹን ይዞ፣ ለተወሰነ ጊዜ ለመኖር ወደ ሞዓብ አገር ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በእስራኤል አገር መሳፍንት ይገዙ በነበረበት ዘመን በሀገሩ ላይ ረሀብ ሆነ፤ ከዚህም የተነሣ በይሁዳ ክፍለ ሀገር ከቤተልሔም አንድ ሰው ከሚስቱና ከሁለት ወንዶች ልጆቹ ጋር ለመኖር ወደ ሞአብ አገር ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እንዲህም ሆነ፥ መሳፍንት ይፈርዱ በነበረ ጊዜ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር በሞዓብ ምድር ሊቀመጥ ከቤተ ልሔም ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እንዲህም ሆነ፤ መሳፍንት ይፈርዱ በነበረ ጊዜ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር በሞዓብ ምድር ሊቀመጥ ከቤተ ልሔም ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሩት 1:1
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በምድርም ራብ ሆነ፥ አብራምም በዚያ በእንግድነት ይቀመጥ ዘንድ ወደ ግብጽ ወረደ፥ በምድር ራብ ጸንቶ ነበርና።


በምድርም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ራብ ላይ ራብ ሆነ፥ ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤም ንጉሥ ወደ አቢሜሌክ ወደ ጌራራ ሄደ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ምድር ባለመታመን በእኔ ላይ ኃጢአት ብትሠራ፥ እጄን እዘረጋባታለሁ፥ የምግቧንም በትር እሰብራለሁ፥ ራብን እሰድድባታለሁ፥ ሰውንና እንስሳንም ከእርሷ አጠፋለሁ፤


ይህም ሰው ሌላ መኖሪያ ስፍራ ለመፈለግ ከተማይቱን ለቆ ሄደ። በሚጓዘበትም ጊዜ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር ወዳለው ወደ ሚካ ቤት መጣ።


የኃይላችሁንም ትዕቢት እሰብራለሁ፤ ሰማያችሁንም እንደ ብረት፥ ምድራችሁንም እንደ ናስ አደርጋለሁ።


ራቡ አሁንም በምድሪቱ ላይ እንደ ጸና ነበር፤


“እኔ በከተማችሁ ሁሉ ራብን፥ በስፍራችሁም ሁሉ እንጀራን ማጣት አመጣባችኋለሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።


በምድር ላይ ራብን ጠራ፥ የእህልን ኃይል ሁሉ ሰበረ።


“በእርሻ ላይ ብዙ ዘር ትዘራለህ፤ አንበጣ ስለሚበላው የምትሰበስበው ጥቂት ይሆናል።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን ሰይፍ፥ ራብ፥ ክፉ አውሬና ቸነፈር፥ ሰውንና እንስሳን ከእርሷ ለማጥፋት ብሰድድም፥


ወደ ኤርምያስ ስለ ድርቅ የመጣው የጌታ ቃል ይህ ነው።


ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ ፍሬያማዋን ምድር ጨው አደረጋት።


ኤልያስም በታዘዘው መሠረት ወደ አክዓብ ሄደ፤ በዚህ ጊዜ በሰማርያ ረሀብ እጅግ ጸንቶ ነበር።


ከዮፍታሔ ቀጥሎ የቤተልሔሙ ኢብጻን በእስራኤል ላይ ፈራጅ ሆነ።


በዳዊት ዘመነ መንግሥት፥ በተከታታይ ለሦስት ዓመት ራብ ሆነ፤ ስለዚህ ዳዊት ጌታን ጠየቀ፤ ጌታም፥ “ሳኦል ገባዖናውያንን ስለ ገደለ፥ እርሱና ቤቱ የደም ዕዳ አለባቸው” አለ።


በይሁዳ ምድር፥ በይሁዳ ነገድ መካከል በቤተልሔም የሚኖር አንድ ሌዋዊ ወጣት ነበር።


ስለዚህ ወላጂቱ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፤ ከዚህ በኋላ የቀሩት ወንድሞቹ ወደ እስራኤል ልጆች ይመለሳሉ።


የቤተልሔም አባት ሰልሞን፥ የቤት-ጋዴር አባት ሐሬፍ።


የሰልሞንም ልጆች ቤተልሔም፥ ነጦፋውያን፥ ዓጣሮት-ቤት-ዮአብ፥ የመናሕታውያን እኩሌታ፥ ጾርዓውያን ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች